News

News Details

Featured

የኮርፖሬሽኑ አመራሮች ጊዜውን የዋጀ አመራር ለመስጠት የሚረዳ ስልጠና መውሰድ ጀመሩ

የኮርፖሬሽኑ አመራሮች ጊዜውን የዋጀ አመራር ለመስጠት የሚረዳ ስልጠና መውሰድ ጀመሩ

የኮርፖሬሽኑ አመራሮች ጊዜውን የዋጀ አመራር ለመስጠት የሚረዳ ስልጠና መውሰድ ጀመሩ

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ከፍተኛ እና መካከለኛ አመራሮች ተቋሙን በተለዋዋጭ ዓለማዊ ሁኔታ ውስጥ ውጤታማ በሆነ አግባብ ለመምራት የሚረዳ ስልጠና መውሰድ ጀመሩ፡፡

ስልጠናው ተለዋዋጭ በሆነ ዓለማዊ ሁኔታ ውስጥ መሪዎች እንዴት ጊዜውን የዋጀ አመራር መስጠት ይችላሉ በሚለው ጽንሰ ሀሳብ ዙሪያ የተደራጀ መሆኑን የገለጹት የኮርፖሬሽኑ ዋና ስራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ጃለኔ ሀሰን ተሳታፊዎች ስልጠናውን በአግባቡ ከተከታተሉ ብዙ ቁምነገር እንደሚገበዩ ጠቁመዋል፡፡

ፈጠራ በታከለበት እና ዓለማዊ ሁኔታን ከግምት ውስጥ በማስገባት ውጤት ተኮር ስልጠና ለመስጠት የሚረዱ ስልቶችን ለመተግበር ስልጠናው እንደሚያግዝ የገለጹት የኢትዮጵያ ኢንተርፕርነርሺፕ ልማት ኢንስቲትዩት ዋና ስራ አስፈጻሚ ዶ/ር ሀሰን ሁሴን ስልጠናው ሰልጣኞችን የሚያነቃቃ፣ አስተሳሰባቸውን የሚፈትን እና በሂደት ውስጥ አዲስ ሀሳብ እንዲገበዩ የሚረዳ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ስልጠናውን በኢንዱትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የኢንዱስትሪ ፕሮጀክቶች አገልግሎት ከኢትዮጵያ ኢንተርፕርነርሺፕ ልማት ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር የተዘጋጀ ሲሆን ፈጠራ የታከለበት ፣ጊዜውን የዋጀ እና ውጤታማ አመራር ለመስጠት የሚረዱ ተግባራዊ ስልቶች በተግባር የሚከወንበት አውድ ይፈጥራል ተብሎ ይታመናል፡፡

የኢንዱስትሪ ፕሮጀክቶች አገልግሎት በኢትዮጵያ በማማከር እና በማሰልጠን ለግማሽ ምዕተ ዓመት ገደማ በሀገራዊ ፕሮጀክቶች ላይ ደማቅ አሻራ ማሳረፍ የቻለ አንጋፋ ተቋም ነው፡፡

የኢትዮጵያ ኢንተርፕርነርሺፕ ልማት ኢንስቲትዩት ኢትዮጵያ ከልማታዊ መንግስት እሳቤ ወደ ኢንተርፐርነሪያል መንግስት እሳቤ ያደረገቸውን ሽግግር በመደገፍ ላይ ያለ መንግስታዊ ተቋም ነው፡፡
ምንጭ፡ IPDC (ቴሌግራም https://t.me/ipdcofficial )

 

Industrial Park Investment Development

Related News

No related articles at the moment.