News

News Details

Featured

ኢትዮጵያ ከሶላር ሴል ኤክስፖርት ብቻ ከ900 ሚሊየን ዶላር በላይ በሚቀጥለው አመት ታገኛለች- ጠቅላይ ሚኒስቴር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር)

ኢትዮጵያ ከሶላር ሴል ኤክስፖርት ብቻ ከ900 ሚሊየን ዶላር በላይ በሚቀጥለው አመት ታገኛለች- ጠቅላይ ሚኒስቴር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር)

ዝርዝር መግለጫ፡

ኢትዮጵያ ከሶላር ሴል ኤክስፖርት ብቻ ከ900 ሚሊየን ዶላር በላይ በሚቀጥለው አመት እንደምታገኝ ጠቅላይ ሚኒስቴር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህንን የገለጹት ዛሬ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስትን የስድስት ወራት አፈጻጸም ባቀረቡበት ወቅት ነው፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሀዋሳ ልዩ ኢኮኖሚ ዞን ውስጥ ከስድስት ወራት በፊት ስራ የጀመረው የጃፓኑ ቶዩ ሶላር ኩባንያ ብቻ በበጀት አመቱ የመጀመሪያ አጋማሽ ከ66 ሚሊየን የአሜሪካን ዶላር በላይ የሶላር ሴል ለዓለም ገበያ ማቅረቡን ጠቁመዋል፡፡

ምንጭ :- IPDCበቴሌግራም ቻናል -( https://t.me/ipdcofficial )

ኢትዮጵያ ትርጉም ያለው ለውጥ ሊያመጡ የሚችሉ ባለሀብቶችን ለይታ ለመሳብ ባደረገችው ጥረት ባለፉት ስድስት ወራት አምስት  የሶላር ሴል አምራች ኩባንያዎችን የሳበች ሲሆን ከኒዚህ ኩባኒያዎች ምርት ብቻ በሚቀጥለው ዓመት ሀገሪቱ 900 ሚሊየን የአሜሪካን ዶላር ከኤክስፖርት ታገኛለች ብለዋል፡፡

በሀዋሳ ልዩ ኢኮኖሚ ዞን ከቶዩ ሶላር በተጨማሪ አሪጅን ሶላር እና ካናድያን ሶላር የተባሉ ኩባኒያዎች ስራ የጀመሩ ሲሆን ሎሎች የሶላር ኩባኒያዎች የኢንዱሰትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን በሚያስተዳድራቸው የተለያዩ ልዩ ኢኮኖሚ ዞኖች ወደ ስራ ለመግባት በሂደት ላይ ናቸው፡፡ 

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ኢትዮጵያ ታምርት በሚለው ሀገራዊ እንቅስቃሴ ባለፉት ሶስት ዓመታት የኢንደስትሪዎች የማምረት አቅም ከ44 በመቶ ወደ  66.3 በመቶ ማደጉን ጠቁመዋል፡፡ 
ጠቅላይ ሚኒትሩ በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ አምራች ኢንዱትሪዎች ቆጠራ መካሄዱን ጠቁመው በዚህም ከ413 ሺ አምራች ኢንዱስትሪዎች መኖራቸውን ታውቋል ብለዋል፡

Industrial Park Investment Development

Related News

No related articles at the moment.