የኢንዱስትሪ ፕሮጄክቶች አገልግሎት ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ሺፈራው ሰለሞን የማኔጅመንት ስርዓት ISO 9001:2015 የብቃት መረጋገጫ ሰርቲፊኬት (Certificate) በዛሬው እለት በSAPPHIRE Addis Hotel በተካሄደ ስነስርዓት ከክብርት ኢንጂነር መዓዛ አበራ የኢትዮጵያ ተስማሚነት ምዘና ኢንተርፕራይዝ ዋና ስራ አስፈጻሚ እጅ ተቀብለዋል፡፡ በፕሮግራሙ ላይ ምርትና አገልግሎት በተቀመጠው አለማቀፍ የአሰራር ስርዓት ጥራት ማስጠበቅ ስለሆነ የአለማቀፍ ገበያው የሚጠይቀው ቅድመ ሁኔታ መሆኑን በማውሳት በኢፕአ በኩል የተሰራው ስራ በጣም ጥሩ መሆኑኑና የአመራሩና የሰራተኛው ቁርጠኝነት ውጤት መሆኑን በመግለጽ ሰርቲፊኬቱን ስራ ላይ በማዋል እንድታስቀጥሉት አደራ ብለዋል፡፡
የቢዝነስ ልማትና ፕሮጀክት ማኔጅመንት መምርያ ኃላፊ አቶ ባዬ አስፋው በበኩላቸው እንኳን ደስ አላችሁ በማለት ንግግር ያደረጉ ሲሆን፣ኢፕአ የጥራት አስተዳደር ስርዓትን ለመተግበር የሄደበትን ጥረት በዝርዝር ከቀረቡ በኃላ በራሳችን አቅም የሰራነው በመሆኑ ብዙ ልምድ የተገኘበት ነበር ብለዋል፣ ኢፕአ ከ42 ዓመት በላይ ልምድ ያካበተና አለም አቀፍ ስታንዳርድን የሚከተል፣ ጥራት መለያው የሆነ ድርጅት ነው በማለት አብራርተዋል፡፡
በመጨረሻም አቶ ሽፈራው ሰለሞን የመዝጊያ ንግግር ፕሮግራሙ ተጠናቋል፡፡
ኢፕአ የ ISO 9001:2015 የብቃት መረጋገጫ ሰርቲፊኬት ተቀበለ
Industrial Park
Investment
Development